ባህር ዳር —
የዜጎችን ጥቃት ለመከላከል ህጉ በሚፈቅደው ልክ ከፌዴራል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት ገለፀ።
በቤንሻንጉል ክልል ባሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በተደደጋጋሚ የሚፈፀመው ጥቃት እየከፋ መምጣቱ እንዳሳሰባቸውም አስታውቋል።
በቅርቡ በተደረገ ውይይት በክልሉ የፀጥታ መዋቅር ላይ የአማራ ብሄር ተወላጆች ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ የጋራ ሥምምነት ላይ መደረሱንም የአማራ ክልል ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።