በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተፈናቃዮች አቤቱታ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በመተከል ዞን ቻግኒ ከተማ ውስጥ ራንች በተሰኘ አካባቢ ሜዳ ላይ የሰፈሩ ተፈናቃዮች በረሃብ እየተሰቃየን ነው ብለዋል።

በየጊዜው የሰብዓዊ ድጋፍ በመኪና ተጭኖ ቢመጣም የሚያከፋፍለን አካል የለም ብለዋል። ችግሩ የተፈጠረው በመንግሥት መዋቅር በሚሰጠው ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ተሰብስቦ የሚመጣውን እርዳታ ግለሰቦቹ እኩል ማከፋፈል ባለመቻላቸው ነው ሲል በቅርቡ የሚገኘው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ገልፆል።

የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራም እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን በበኩሉ በክልሉ ከ250ሺ በላይ ተፈናቃይ ይገኛል ሁሉንም እኩል እየተስተናገዱ ነው ብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተፈናቃዮች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00


XS
SM
MD
LG