በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤልጂየም የሉሙባን ጥርስ ለቤተሰባቸው አስረከበች

በኮንጎ የመጀመሪያው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት እና በነብሰ ገዳይ የተገደሉት መሪ የፓትሪስ ሉሙምባ ጥርስ የቤልጅየም መንግሥት በዛሬው ዕለት ብራስልስ ውስጥ በተዘጋጀ የኦፊሴልሥነ ሥርዓት ላይ ለሉሙምባ ቤተሰብ አስረከበ።

ሉሙምባ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1960 በኮንጎ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የተመረጡ እና በአገሩ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው ቢሆኑም በአውሮፓ እና አሜሪካ ኃያላን ብዙም አልተወደዱም ነበር።

ኮንጎ የቤልጂየም ቅኝ ግዛት የነበረች አገር ነች።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960 ቃለ መሃላ በፈጸሙበት ሥነ ስርዓት ሉሙምባ የኮንጎ ህዝብ በቤልጂየም ቅኝ ገዥዎች አስተዳደር ስር በነበረበት ወቅት የደረሰበትን ግፍ በዝርዝር በመናገር በጊዜው በሥነ ስርዓቱ በቦታው የነበሩትን የቤልጂየሙን ንጉስ ባውዶይን አስቆጥተው ነበር።

ኮ/ል ጆሴፍ ሞቡቱ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን ሲጨብጡ ሉሙምባ ሥልጣን የቆዩበት ጊዜ አንድ ዓመት አልሞላም።

መፈንቅለ መንግስቱ ከተፈጸመ ብዙም ሳይቆይ ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እሩምታ ተኩስ ከፋች ቡድን ገጥሟቸዋል። የቤልጂየሙ የፖሊስ መኮንን ጄራርድ ሶኤቴ እና ወንድማቸው የሉሙምባን አስከሬን እንዴት እንደቆራረጡና ደብዛው እንዳይገኝ ለማድረግ የተጠቀሙበትን ዘግናኝ ድርጊት እንደዘረዘሩት ሲል፡ “የሉሙምባ ግድያ” የተባለው መጽሐፍ ደራሲ ቤልጂያዊው ጸሐፊ ሉዶ ዴ ዊት ዘግቧል።

ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1999 ገዳዩ መኮንን ሶኢቴ የሉሙምባን የወርቅ ጥርስ በእጁ እንደሚገኝ አምኖ ነበር።

XS
SM
MD
LG