በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤልጂየም ዓለም አቀፍ እጽ አዘዋዋሪዎች ላይ ክስ ከፈተች


በታሪክ በአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች ላይ ከተደርጉ ክሶች ከፍተኛው ነው የተባለ የክስ ሂደት ቤልጂየም ዛሬ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡

እጽ በማዘዋወር ተሳትፈዋል የተባሉ ከ120 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ አገራት ዜጎች፣ በፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ቆመዋል ተብሏል።

ክሱ የመጣው፣ ተከሳሾቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ የሚስጥር መልዕክት ማስተላለፊያ ማኅበራዊ መገናኛ መድረኮችን መርማሪዎች ሠብረው መግባት እና መልዕክቶቹን መጥለፍ መቻላቸውን ተከትሎ ነው።

ከቤልጂየም፣ አልባንያ፣ ኮሎምቢያ እና ሰሜን አፍሪካ ናቸው የተባሉት ተከሳሾች፣ ብራስልስ በሚገኘው የቀድሞው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰየመው ፍ/ቤት በከፍተኛ ጥበቃ ሥር እንደተሰበሰቡ ታውቋል።

ተከሳሾቹ፤ ኮኬይን እና አሺሽ፣ ከደቡብ አሜሪካ እና ሞሮኮ በማስነሳት ቤልጂየም፣ ኔዘርላንድ፣ ጀርመን እና ጣሊያን በሚገኙ ወደቦች በኩል ማስገባታቸውን ክሱ አመልክቷል።

ቤልጂየም የሚገኘው የአንትወርፕ ወደብ ወደ አውሮፓ የሚላክ ኮኬይን ዋና መግቢያ እንደሆነ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG