በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሣይ የጀመረው ተቃውሞ ወደ ቤልጂየም ተዛምቷል


ብራስልስ፣ ቤልጂየም
ብራስልስ፣ ቤልጂየም

አንድ የ17 ዓመት ሹፌር በፖሊስ መገደልን ተከትሎ በፈረንሳይ የተነሳው ተቃውሞ ወደ ቤልጂየምም ተዛምቶ ለሶስተኛ ምሽት ቀጥሏል።

ግድያው በተፈጸመባት ናንቴር ከተማ ተቃዋሚዎች መንገድ በመዝጋት እሳት ሲያነዱ፣ መኪኖችንም አቃጥለዋል። ፖሊስ በበኩሉ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል።

ከ600 መቶ በላይ ተቃዋሚዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ቢያንስ 200 የሚሆኑ የፖሊስ አባላት ተጎድተዋል ተብሏል።

በሌሎች የፓሪስ አካባቢዎችም ተቃዋሚዎች አንድ የአውቶብስ ተራ እና የከተማ ማዘጋጃ ቤት ሲያቃጥሉ፣ ሱቆችንም ዘርፈዋል።

የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዒማኑኤል ማክሮን በብራስልስ የታደሙበትን የአውሮፓ ኅብረት ጉባኤ አቋርጠው ዛሬ ወደ ፈረንሳይ በመመለስ ከባለሥልጣኖቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።

ናኤል የተባለውን የ 17 ዓመት የጥቅል ማጓጓዣ መኪና ሾፌር ገደሏል የተባለው ፖሊስ በነፍስ ማጥፋት መከሰሱን አቃቤ ሕግ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG