ቤላሩስ የሩሲያን የኒዩክለር ጦር መሳሪያ በቋሚነት በግዛቷ ውስጥ እንዲተከል መስማማቷን ዛሬ በሰጠችው ህዝብ ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ማጽደቋን አስታውቃለች፡፡
በዛሬ እለት ተቀልብሷል የተባለው ነባር ህግ የቤላሩስን ገለልተኝነት የሚሽር ሲሆን ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጠንካራ ወታደራዊ ልምምድ በር ይከፍታል ተብሏል፡፡
ባለፈው ሀሙስ በወታደራዊ ልምምድ ሰበብ ወደ ዩክሬን የሄዱት የሩሲያ ወታደሮችም ከዚሁ ከቤላሩስ የተንቀሳቀሱ መሆናቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡
ለውጡ ቤላሩስ ከሶቭዬት ህብረት ነጻ ከወጣች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዛቷ የኒውክለር መሳሪያ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በተያያዘ ዜናም ዩናትይድ ስቴትስ በቤላሩስ ያላትን የኤምባሲ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡