በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ" - አቶ በቀለ ነጋ


ፎቶ ፋይል፡ አቶ በቀለ ነጋ
ፎቶ ፋይል፡ አቶ በቀለ ነጋ

በፓርቲያቸው ስም ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳይሰጡ፣ ከቤት እንዳይወጡና ሥራ እንዳይሠሩ ከተደረጉ አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር እንደተቆጠረ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

“ከዚህ በላይ መብቴ ሊነካ አይገባም፣ ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ” ብለዋል።

ፓርቲያቸው አባል የሆነበት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሚገኙበትን ሁኔታ ጠቅሶ ደብዳቤ ጽፎ ቢጠይቅም አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል መታጣቱን ጨምረው ተናግረዋል።

የፓርቲው ጠበቃ አቶ ወንድሙ ኢብሳ በበኩላቸው "ይህን ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ" የሚል አካል መታጣቱን ተናግረዋል። ሁኔታውን ከፖሊሰ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ" - አቶ በቀለ ነጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:05 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG