በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ለጋዜጠኞች የከፋች ሃገር


ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ ጋዜጠኞች

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም ከባዱ የነበረውን የሶማሊያ ጋዜጠኞች ሥራና ሕይወት ይበልጥ ያወሳሰበው መሆኑን የዓለም የፕሬስ ቀንን አስመልክቶ ለቪኦኤ ሃሣባቸውን ያካፈሉ የሃገሪቱ ጋዜጠኖች ተናግረዋል።
"ሶማሊያ ለጋዜጠኞች ሁል ጊዜም የከፋች ሃገር ነች" ብላል የሶማሊያ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሞሐመድ ኢብራሂም ሙአሊሚ ከሶማሊኛ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረባ ሞሐመድ ኦላድ ጋር ዛሬ ባደረገው ውይይት።
በዚህ ዓመት ግን በተለይ ሃገራችን በኮሮናቫይረስ ሥርጭት ውስጥ ባለችበት ጊዜ ባለሥልጣናቱ ጋዜጠኞችን ማዋከባቸውን አጠናክረዋል ብሏል። ሦስት ጋዜጠኞች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በዘፈቀደ መታሰራቸውን፤ አንድ የራድዮ ጋዜጠኞ ከሥራው መታገዱን የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ አክሎ ጠቁማል።

XS
SM
MD
LG