ቤጂኒግ በቻይና ምንም እንኳ የአዳዲስ ኮቪድ ተጋላጮች ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም እያንሰራራ ለሚገኘው የኮቪድ-19 የሚውሉ አዳዲስ የሆስፒታል ተቋማትን እያዘጋጀች መሆኑን አስታወቀች፡፡
የቻይና መንግሥት ዛሬ እንዳስታወቀው በሰሜን ምስራቅ ቻይና በዚዮታንግሻን ግዛት ውስጥ እኤአ በ2003 ለሳርስ ወረርሽኝ የተዘጋጀውን ሆስፒታል ለኮቪድ-19 እንዲውል እንደገና መታደሱን አስታውቋል፡፡ የቻይና የዚሮ ኮቪድ ፖሊሲዋን ለመጠበቅ ጉዞዎችን የምትገድብ።
የጅምላ ክትባቶችን በከተሞች የምትሰጥና ጊዚያዊ የህክምና መስጫ ተቋማትን አስቀድማ የምታዘጋጅ መሆኑን ተነገሯል፡፡ በቤጂንግ የአዲስ ተጋላጮች ቁጥር ባለበት የቀጠለ ሲሆን ትናንት ሰኞ 62 የሚደርሱ አዳዲስ ተጋላጮች የተመዘገቡ ሲሆን ከዚያ ውስጥ 11ዱ ምንም ዓይነት ምልክት ያልታየባቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡