በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስቲንግ ገዢዎች ቦርድ ሊቀ መንበር ሩስያ እንዳይገቡ ተከለከሉ


ፋይል- የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስቲንግ ገዢዎች ቦርድ ሊቀ መንበር ጄፍ ሸል
ፋይል- የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስቲንግ ገዢዎች ቦርድ ሊቀ መንበር ጄፍ ሸል

በሥራ ጉዳይ ወደ ሞስኮ የሄዱት የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስቲንግ ገዢዎች ቦርድ ሊቀ መንበር ጄፍ ሸል ሩስያ እንዳይገቡ መከልከላቸውና በአውሮፕላን ማረፊያው ለበርካታ ሰዓታት በቁጥጥር ሥር መቆየታቸው ታወቀ።

የአሜሪካ ድምፅ እና የሬድዮ ፍሪ አውሮፓ አስተዳዳሪና የኤጀንሲው ሊቀ መንበር ጀፍ ሸል ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንደተናገሩት ሞስኮ እንደደረሱ በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ከተሰለፉበት የኢሜግሬሽን መሥመር እንዲወጡ ታዘው በጥበቃ ሥር እንዲቆዩ ተደርገዋል።
ፖሊሶች በሩሲያ ቋንቋ በተጻፈ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ የጠየቋቸው መሆኑንና እርሣቸውም ሊረዱት በማይችሉት ነገር ላይ አልፈርምም ሲሉ መመለሳቸውን ተናግረዋል።በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ የቀረበላቸው ሰነድ ደግሞ ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ የተከለከሉ መሆናቸውን እንደሚገልጽ አስረድተዋል።
ባለሥልጣናቱ ወደ ሩስያ እንደይገቡ የተከለከሉበትን ምክንያት እንዳልገለጹላቸውና ለሌላ ተጨማሪ ሦስት ሰዓታት በጥበቃ ሥር እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ ባዘጋጁላቸው በረራ ከሞስኮ መውጣታቸውን፥ የዩናይትድ ስቴትስ ብሮድካስቲንግ ገዢዎች ቦርድ ሊቀ መንበር ጀፍ ሸል ሁኔታውን አብራርተዋል።
XS
SM
MD
LG