በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ደምበል ሐይቅ ላይ የጥምቀት ከተራ በዓል በኃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዐቶች ተከብሯል። የገዳማቱ ዕድሜ ጠገብ መኾንና በዓሉ በሐይቁ ላይ መከበሩ የተለየ ውበትና ትርጉም እንደሚሰጠው፣ በደሴቶቹ ላይ የሚገኙት ቤተ ክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ዲያቆን ዘነበ ዋቆ ተናግረዋል። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ አለሙ በዳዶም፣ ታቦታቱ በተለይ ውሃው ላይ ሲገናኙ የሚፈጥረዉ ስሜት ልዩ መኾኑን ገልጸዋል።
የበዓሉን ድባብ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም