በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ (ቢኤኤል)


የሞዛምቢክ እና የሴኔጋል የቅርጫት ኳስ ቡድኖች መካከል የተደረገ ጨዋታ
የሞዛምቢክ እና የሴኔጋል የቅርጫት ኳስ ቡድኖች መካከል የተደረገ ጨዋታ

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ እአአ በግንቦት 2021 በይፋ የተጀመረ ከአፍሪካ አህጉር የተውጣጡ የቅርጫት ኳስ ክለቦች የሚወዳደሩበት ስፓርታዊ መድረክ ነው። ሊጉ የአሜሪካ ብሄራዊ ቅርጫት ኳስ ማኅበር እና የዓለም አቀፉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የትብብር መርኃግብር ነው። በታላላቅ የንግድ ድርጅቶችም ይደገፋል።

በዚህ መርኃግብር በየሀገራቸው ካሉ ቡድኖች ልቀው የተገኙ 12 ቡድኖች ይወዳደራሉ። የመጀመሪያው ውድድር የተከናወነው በሩዋንዳ ኪጋሊ የስፖርት ማዕከል ሲሆን፣ የውድድር ምዕራፉ አሸናፊ የግብፁ ዛማሊክ ክለብ ነበር።

የዘንድሮ(2014/2022) የውድድር ዘመን ጨዋታዎች ከየካቲት 14 ግንቦት 20/2014 በሦስት የአፍሪካ ከተሞች ይካሄዳሉ። የሳህራ ምድብ በተባለው ስር የተደለደሉ ስድስት ቡድኖች ሴኔጋል ዳካር ላይ እስከ መጋቢት 6/2014 ባለው ጊዜ ተጨውተዋል። ከሚያዚያ 1-11/2014 ደግሞ በናይል ምድብ ውስጥ የተደለደሉ ስድስት ቡድኖች ግብፅ ካይሮ በሚገኘው የዶ/ር ሀሰን ሙስጦፋ የስፖርት ማዕከል ውድድሮችን ያከናውናሉ።

ከሁለቱ ምድቦች የተመረጡ አራት አራት ቡድኖች ለጥሎ ማለፍ ፉክክር ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ ይገናኛሉ። የፍጻሜው ውድድር ግንቦት 20/2014 በሩዋንዳ ኪጋሊ የስፖርት ማዕከል ይካሄዳል።

በዘንድሮው ውድድር ተፎካካሪ የሆኑት ክለቦች የመጡባቸው ሀገራት፣ ሞሮኮ፣ አንጎላ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ፣ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ ጊኒ፣ ካሜሮን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ደበቡ ሱዳን ናቸው።

እስካሁን በተደረገው የሳህራ ምድብ ጨዋታ የሩዋንዳዊ አር ኢጂ፣ የቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስሪኒ፣ የሞሮኮው ኤኤስዲ ሳሊ እና የጊኒው ኤስኤለ አትሌቲክ ለጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

XS
SM
MD
LG