በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞዪቱ ቀዳሚት እመቤት ባርብራ ቡሽ አስከሬን ቀብር ከነገ በስተያ ቅዳሜ ይፈፀማል


የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞዪቱ ቀዳሚት እመቤት ባርብራ ቡሽ
የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞዪቱ ቀዳሚት እመቤት ባርብራ ቡሽ

በዘጠና ሁለት ዓመት ዕድሜአቸው ማረፋቸው ትናንት የተነገረው የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞዪቱ ቀዳሚት እመቤት ባርብራ ቡሽ አስከሬን ቀብር ከነገ በስተያ ቅዳሜ እንደሚፈፀም ተነግሯል።

በዘጠና ሁለት ዓመት ዕድሜአቸው ማረፋቸው ትናንት የተነገረው የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞዪቱ ቀዳሚት እመቤት ባርብራ ቡሽ አስከሬን ቀብር ከነገ በስተያ ቅዳሜ እንደሚፈፀም ተነግሯል።

የቴክሳሷ ከተማ ህዩስተን የባርብራ ቡሽን ሕይወትና ቅርስ በማክበርና በመዘከር ላይ ስትሆን ትናንት ምሽትና ሌሊቱን የከተማዪቱ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ ይወድዱት በነበረ ቀለማቸው ሰማያዊ ብርሃን አሸብርቆ እንደነበር ታውቋል።

የሚስ ቡሽ አስከሬን ነገ፤ ዓርብ እርሣቸውና አርባ ሁለተኛው ፕሬዚዳንት ባለቤታቸው ጆርጅ ቡሽ ያዘወትሩባት በነበረ ኤጲስቆጶሳዊት ቤተክርስትያን አርፎ ለሕዝብ ስንብት ክፍት ይሆናል።

ግርማ ሞገስ የተላበሱት የፖለቲካ ሥርወ መንግሥት እናት - ባርብራ ቡሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG