ዋሺንግተን ዲሲ —
የባንግላዴሹ ፕሬዚዳንት አብዱ ሀሚድ ያፀደቁት አዲስ ህግ፣ "የመናገር እና የፕሬስ ነፃነትን ይገድባል" ሲሉ፣ የመገናኛ ብዙኃን ድርጅቶችና ሃያስያን አሳሰቡ።
የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ጆይናል አበዲን ናቸው ይህን በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉት።
አዲስ የወጣው ህግ፣ ቀደም ያለውን የቴክኖሎጂና የኢንፎርሜሽን ሥርጭት መመሪያ የሚተካ እንደሆነም ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ