ከሁለት ወራት በፊት በባልትሞር ከሚገኘው ‘ፍራንስስ ስካት ኪ ብሪጅ’ ጋራ የተጋጨችው የዕቃ ጫኝ መርከብ ዛሬ እንድትንቀሳቀስና ወደ ወደብ እንድታመራ ተደርጓል።
‘ዳሊ’ በሚል ሥም፣ የምትጠራው መርከብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት ከድልድዩ ጋራ ስትጋጭ፣ በድልድዩ ላይ የነበሩ ስድስት የግንባታ ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከፍተኛ የመርከብ እንቅስቃሴ የሚያስተናግደው የባልትሞር ወደብ በአብዛኛው ዝግ እንዲሆንም አድርጓል።
መርከቢቱ እንድትንቀሳቀስ መደረጉ በፍርስራሽ የማጽዳትና የፍለጋ ሂደቱ ትልቅ ክንውን ነው ተብሏል።
‘ዳሊ’ በበርካታ መሪ ጀልባዎች ዛሬ ማለዳ እንድትንቀሳቀስ መደረጉ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም