ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃትንና ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር መጣሷን በመቃወም ሰላማዊ እንደሚካሄድ ገልፆ ለእሁድ ዕለት በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ፖሊስ ኮሚሽኑ ዛሬ እንዳስታወቀው ሰልፉ ተቀባይነት እንዳላገኘ ለባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ መፃፉን ገልጾ ነገር ግን ከዚሁ በተቃራኒ ሰልፉ እንደሚደረግ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተገለፀ ይገኛል ብሏል።
ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በሕግ ተጠያቂ ያደርጋል ሲልም አሳስቧል። ባልዳራስ ሰልፉን ለማካሄድ የሚስፈልገውን እውቅና ለማግኘት ለሚመለከተው አካል ማመልከቻ ማስገባቱን መግለፁን በትላንትናው ምሽት መዘገባችን ይታወሳል።