በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጤፍን ጨምሮ በሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ መናር ተማረዋል


የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጤፍን ጨምሮ በሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ መናር ተማረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:14 0:00

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጤፍን ጨምሮ በሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ መናር ተማረዋል

ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋው እየጨመረ የመጣው የጤፍ እና የሌሎች መሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መናር እንዳሳሰባቸው፣ በባሕር ዳር ከተማ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች እና ሸማቾች ገለጹ፡፡

ባለፈው ስድስት ወር ብቻ፣ ጤፍ ከነበረበት አምስት ሺሕ ብር በእጥፍ እንደጨመረ የሚናገሩት ነጋዴዎች እና ሸማቾች፤ የቁጥጥር ማነስ፣ የጥቁር ገበያ መስፋፋት እና በቅርቡ በስፋት የተከሠተው የማዳበሪያ እጥረት፣ ለዋጋ ንረቱ መንሥኤዎች እንደኾኑ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል፡፡

በመሠረታዊ ሸቀጦች ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል የሚታየው አለመጣጣም፣ የጤፍን ዋጋ ጨምሮ ለመሠረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት ምክንያት እንደኾነ የሚናገሩት የኢኮኖሚ

ባለሞያው አቶ ይርጋ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ መንግሥት፣ በተለይ የግብርና ምርቶችን አቅርቦት በማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት አመልክተዋል።

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG