በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዳበሪያ እጥረት የዘር ወቅት ያለፈባቸው የምዕ.ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ለሦስተኛ ጊዜ ሰልፍ ወጡ


በማዳበሪያ እጥረት የዘር ወቅት ያለፈባቸው የምዕ.ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ለሦስተኛ ጊዜ ሰልፍ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:07 0:00

በማዳበሪያ እጥረት የዘር ወቅት ያለፈባቸው የምዕ.ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ለሦስተኛ ጊዜ ሰልፍ ወጡ

በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ፣ መሸንቲ በሚባል አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች፣ የማዳበሪያ እጥረት እንደገጠማቸው፣ በባሕር ዳር ከተማ በድጋሚ ባካሔዱት ሰልፍ ገለጹ።

አርሶ አደሮቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ማዳበሪያ በወቅቱ ባለማግኘታቸው ማሽላ አለመዝራታቸውንና ለማሽላ በአዘጋጁት መሬት፣ ጤፍ እና ዳጉሳ ለመዝራት መሬቱን አለስልሰው ቢጠብቁም፣ በማዳበሪያ እጥረት ወቅቱ እያለፈባቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

በዐማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች፣ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እንዳለ፣ ከአርሶ አደሮች ማረጋገጥ ያቻልን ሲኾን፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ በባሕር ዳር ከተማ ጅራፍ እያጮኹ ሰልፍ ሲወጡ፣ የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከዐማራ ክልል ግብርና ቢሮ፣ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ የግብርና ሚኒስቴር፣ ዛሬ በፌስቡክ ገጹ እንዳስነበበው፣ 7ነጥብ4 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ በጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲኾን፣ ከዚኽ ውስጥ 6ነጥብ6 ሚሊዮን ኩንታሉ፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው፤ ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG