በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰኔ 2011 የባሕር ዳር ግድያ በተከሰሱ ላይ ብይን ተሰጠ


በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት በተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ ብይን ሰጥቷል።

በነመማር ጌትነት የክስ መዝገብ ከቀረቡት 55 ተከሳሾች ውስጥ 20ዎቹ በነፃ ሲለቀቁ በ31ዱ ላይ የጥፋተኝኑት ውሳኔ አስተላልፏል።

ጉዳያቸው በሌሉበት ሲታይ ከነበሩት 6 ተከሳሾች ውስጥ ሻምበል መማር ጌትነት በላይ ሰው ሰፊነው እና ልቅናው ይሁኔ በተባሉ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል።

ለሁለት ዓመት ያህል ምርመራውን ሲያደር የቆየው የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት በተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ከተከሳሾቹ ውስጥ 6ቱ ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ ሲሆን 31ዱ ጥፋተኛ ናቸው ሲል 20ዎቹን ደግሞ በነፃ አሰናብቷል።

ለብይኑ መነሻ 74 ምስክሮችን እንደሰማ፣ የግል ተበዳዮች የሕክምና ማስረጃዎችን እንደፈተሸ ከብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት፣ ከፌዴራል እና ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘውን የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃ በግብአት እንደተጠቀመበት ችሎቱ ገልፆል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በሰኔ 2011 የባሕር ዳር ግድያ በተከሰሱ ላይ ብይን ተሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00


XS
SM
MD
LG