በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፀሐይ ጀንበሩ አረፉ


ዶ/ር ፀሐይ ጀንበሩ
ዶ/ር ፀሐይ ጀንበሩ

ከ1997 እስከ 2001 ዓ.ም በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት ዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ከ1997 እስከ 2001 ዓ.ም በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት ዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ዶ/ር ፀሐይ ላለፉት 23 ዓመታት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በመምህርነትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ በጎንደር መምህራን ኮሌጅና በደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ መጽሃፍትን ለአንባብያን ማድረሳቸውንና በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግም ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

ከቀኝ አዝማች ጀምበሩ ተድላና ከእማሆይ ምንትዋብ ገደፋው በደብረ ማርቆስ ከተማ በ1947 ዓ.ም የተወለዱት ዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው፣ ትናንት መጋቢት 9/2010 ዓ/ም በተወለዱ በ63 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡

ዶ/ር ፀሐይ ጀምበሩ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG