በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመፈንቅለ መንግሥቱ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን መንግሥት ገለፀ


ባህር ዳር
ባህር ዳር

ከከሸፈው የቅዳሜ ዕለት መፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ፣ አያሌ ሰዎች መገደላቸውን፣ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታወቀ።

ይህ የቃል አቀባዩ መግለጫ፣ በግጭቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገ ኦፊሴላዊ መረጃ መሆኑ ነው።

አሰማኸኝ አስረስ ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደገለፁት፣ አንድ ከሥርዓት ያፈነገጠ የሚሊሽያ ቡድን በክልሉን የፖሊስ ዋና ጽ/ቤት፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት ቢሮና በክልሉ ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ላይ ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት አድርሷል።

ይህ ሚሊሽያ ቡድን፣ በቅርቡ ከተቋቋመው ከክልሉ የፀጥታና ደኅንነት አገልግሎት አባላት መካከል የተውጣጣ ሲሆን፣ ሌሎችም እንዲቀላቀሉት ጥሪ ሲያቀርብ መሰንበቱን ቃል-አቀባዩ አሰማኸኝ፣ ዛሬ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል አስታውቀዋል።

የክልሉን መንግሥታዊ መገናኛ አውታር በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ያደረገው ሙከራ እንዳላልተሳካለትም ነው አቶ አሰማኸኝ ጨምረው የገለፁት፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG