በኦሮሚያ ክልል ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው በዐማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የሚያስችል ውይይት፣ በባሕር ዳር ከተማ ተካሔደ፡፡
የኦሮሚያ እና የዐማራ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ባካሔዱት ምክክር፣ ተፈናቃዮቹን ሰላም ወደሰፈነባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ኀይሉ አዱኛ እና የዐማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ወንደሰን ለገሰ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ሰላማዊ አካባቢዎች ለመመለስ የሚያስችል ሥራ ከነገአንስቶ እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም