በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው ታሰሩብን" - አብን


የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

"አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው ታሰሩብን" ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ አቤቱታ አሰምቷል።

ሃያ ስምንት እንደሚሆኑ አብን ያሳወቃቸው አባላትና ደጋፊዎቹ የታሠሩት የመሪዎቻቸውን ጉዳይ ለመከታተል አዲስ አበባ፤ አራዳ ምድብ ችሎት ተገኝተው በነበረ ጊዜ መሆኑንም አብን ገልጿል።

“የታሠሩብን ‘አማራነት እና እውነት አይታሰርም’ የሚል ሸሚዝ የለበሱ ናቸው” ሲሉ የንቅናቄው የፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ካሣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የተያዙት ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የሦስት ሺህ ብር ዋስ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውንም አቶ በለጠ አመልክተዋል።

ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው ታሰሩብን" - አብን
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG