በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ወደ ዋይት ሃውስ ተመልሰዋል


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለ72 ሰዓታት ያህል ሆስፒታል ገብተው የታከሙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ማታ ወደ ዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ተመልሰዋል፤ አሜሪካውያን ቫይረሱን እንዳይፈሩ አሳስበዋል።

ወደ ዋይት ሃውስ እንደተመለሱ ብርታታቸውን ለማሳየት ሲሉ ረዥም ደረጃዎችን ወጥተዋል።

በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት የተቀረፀ መልዕክት፤

“ኮቪድ-19ን አትፍሩ፣ ኑሯችሁን እንዲያዳክም አትፍቀዱ” ብለዋል።

አሃዞች በሚያስተላልፉት መሠረት፣ በፕሬዚዳንታዊ ውድድር ጆ ባይደን እየቀደሙ ናቸው። ከአስር ቀናት በኋላ እንዲካሄድ በታቀደው ሁለተኛ ክፍል ክርክር እንደሚሳተፉ፣ የምርጫ ዘመቻው አስተባባሪዎች ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG