በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ የዋቄፈና እምነት መሪዎችን ጨምሮ ከ80 በላይ አማኞች፣ በከተማው ፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን፣ የእምነት ተቋሙ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
የእምነቱ መሪዎች እና ተከታዮች በታሰሩበት ቀን፣ የተቋሙን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ እንደነበሩ፣ የመረጃ እና ሕዝብ ግንኙነት መሪው አቶ ለማ በይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
ታሳሪዎቹ እስከ አሁን ፍርድ ቤት አለማቅረባቸውን አቶ ለማ ጠቅሰው፣ የዞኑ አስተዳደር አካላት በእምነቱ ላይ ጫና እያሳደሩ ነው፤ ሲሉ ከሰዋል፡፡
የባቢሌ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ፣ “ከሃይማኖት ጋራ በተገናኘ በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል የለም፤” ሲል ክሱን አስተባብሏል።
መድረክ / ፎረም