አበዳሪ ሀገራት፣ ለኢትዮጵያ የፈቀዱት የብድር እፎይታ፣ ከጊዜያዊ መፍትሔነት የዘለለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደሌለ፣ የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ፣ ኢትዮጵያ የ1ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር እፎይታ ማግኘቷን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው፣ የተቋማቸውን የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ “መዋቅራዊ የፖሊሲ መፍትሔ ያስፈልገዋል፤” ያሉት ባለሞያዎቹ፣ አኹን ካለበት የተወሳሰበ ችግር አንጻር እፎይታ ቢያገኝም፣ በቀጣይ ጊዜያት ብድሩን ለመክፈል የሚያስችል ተጨማሪ ገቢ የሚያመነጭ እንዳልኾነ አስረድተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም