በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች፣ የጸጉር መሸፈኛ ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ በመከልከሉ ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ቤት አልገቡም" ሲል የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተናገረ።
የምክር ቤቱ ፀኃፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል፣ "ተማሪዎቹ በሃይማኖታዊ አስተምህሮ መሠረት ፀጉራቸውን መሸፈን ስላለባቸው የመማር መብታቸው ሊከበር ይገባል" ብለዋል።
በጉዳይ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የፀጉር መሸፈኛ ሒጃብ አድርገው እንዳይገቡ እንደከለከሉ ስማቸው ከተጠራ ትምህርት ቤቶች አንዱ አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት “ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካ እና ሀይማኖታዊ ይዘቶች ነፃ መሆን ስለሚገባቸው ሁል ጊዜም የሚደረግ ነው” ብሏል።
መድረክ / ፎረም