በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አወሊያና የቀጠለ ውዝግቡ


የእሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የአወሊያ ኮሚቴ ለጥያቃዎችዎ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ዛሬም በአዲስ አበባው አወሊያ ተቋም ውስጥ ከስምንት መቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ሰላማዊ ህዝባዊ ተቃውሞ ማካሄዱን የህዝቡን ጥያቄ ለመንግስት ያቀረበው ኮሚቴ አባል አቶ አህመዲን ጀበል ገልፀውልናል።

የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቁጥሩ የተጋነነ ነው ከማለቱም በላይ የተቃውሞውን መንስዔ አይቀበልም።

ትዝታ በላቸው ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼኽ አህዛም ዩሱፍና በአወሊያ ተቋም ጉዳይ ዙሪያ ከተቋቋመው ኮሚቴ ደግሞ አቶ አህመዲን ጀበልን በሙስሊሙ ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ላይ ታወያያለች።

ሁለቱ እንግዶች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በቅርቡ “የአልቃይዳ ህዋስ በሁለት የኢትዮጵያ ዞኖች ተገኝቷል” ባሉትም ላይ መልስ ይናገራሉ።

ሼኽ አህዛም ተቋሙ ህጋዊ እንደሆነና እርሣቸውም በህጋዊ መንገድ እንደተመረጡ ገልፀዋል፡፡ በአወሊያ ተቋም ዙሪያ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ የቀረቡ ጥያቄዎችን ለመንግሥት የሚያሰማው ኮሚቴ አባል አቶ አህመዲን ጀበል የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች በህዝቡ የተወከለ አይደለም ይላሉ፡፡

ውይይቱን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG