በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዋሽ ወንዝ ሞልቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ


አዋሽ ወንዝ
አዋሽ ወንዝ

በኦሮምያ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ አዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው መጥለቅለቅ ከአስር ሺህ በላይ ሰው ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል።

በደራሽ ውኃ በወረዳው ሦስት ቀበሌዎች ብዙ ቁጥር ያላቸው እንስሣት መደሰዳቸውንና ከአስራ ስምንት ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ ማሳ መውደሙን የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በደረሰው መጥለቅለቅ በውኃ የተከበቡ ዜጎችን ለማስወጣትም ሆነ ድጋፍ ለመስጠት ከመከላከያ ሚኒስቴር ሂሊኮፕተር ተጠይቆ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም ኮሚሽኑ አመልክቷል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አዋሽ ወንዝ ሞልቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG