በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዋሽ ሙላትን ተከትሎ ለተፈነቀሉ የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ እየቀረበላቸው ነው


በኦሮምያ ክልል ሁለት ዞኖች፤ በምስራቅ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች ውስጥ የአዋሽ ወንዝ ሙላትን ተከትሎ ወደ ሃያ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት ቁጥጥር መምሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

በሰው ህይወት እና ከብቶች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የገለፀው ኮሚሽኑ በሁለቱ ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች የአደጋ ግዜ ዕርዳታ እያቀረበ መሆኑ ገልፀዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ አባዲር አብዳ ለቪኦኤ እንደገለፁት፣ የዘንድሮው የአዋሽ ሙላት ባልተለመደ ሁኔታ ያጋጠና ከቆቃ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ የተለቀቀውን ጨምሮ ጉልበቱ የፈረጠመ ቢሆንም ቀድሞ በተሰራ ሥራ በሰው ህይወት ላይ አደጋ እንዳያደርስ መደረጉን ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአዋሽ ሙላትን ተከትሎ ለተፈነቀሉ የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ እየቀረበላቸው ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00


XS
SM
MD
LG