በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራሲ እየተዳከመ አምባገነንነት እየጨመረ ነው

FILE - Police officers disperse people at the closed Victoria Park on the 33rd anniversary of the crackdown on pro-democracy demonstrations at Beijing's Tiananmen Square in 1989, in Hong Kong, June 4, 2022.

ሰዎች በምርጫዎች ተአማኒነት እምነት በማጣታቸውና በተለያዩ ጉዳዮች ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ እንዳይችሉ ገደቦች የተጣሉባቸው በመሆኑ በመላው ዓለም ዴሞክራሲ እየቀነሰ መምጣቱን 34 የዲሞክራሲ አገሮች ውስጥ የተካተቱበት አንድ ድርጅት አስታወቀ፡፡

ዴሞክራሲ እንዲስፋፋ ለማስተዋውቅ የተቋቋመው ዓለም አቀፋዊ ሀሳብ (The International IDEA) የተሰኘው ድርጅት ከዓለም ግማሽ የሚሆኑ የዴሞክራሲ መንግሥታት “ተመራጭ መሪዎቻቸው በሩሲያው የዩክሬን ጦርነት፣ በተወደደው የኑሮ ቀውስ፣ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ውድቀት እንዲሁም የአየር ንብረት ቀውስ የተነሳ” እየተዳከሙ ነው ብሏል፡፡

መቀመጫውን በስዊድን ያደረገው ይህ ድርጅት ዓለም ሰማይ በነካው የኑሮ ውድነት፣ በኒዩክለር ጦር ሥጋትና የዴሞክራሲ አገዛዝ እየጠፋ መርዛማ ነገር የተቀላቀለበት ቀውስ ውስጥ ይገኛል ሲል ገልጿል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ወደ አምባገነንነት የሚያመሩ የዴሞክራሲ አገሮች በእጥፍ እየጨመሩ መሆኑን ሲገልጽ አምባገነን መንግሥት ያላቸው አገሮች ደግሞ የሚያደርሱትን ጭቆና አጠናክረው መቀጠላቸውን ዘገባውን ያጠናቀረው አሶሴይትድ ፕሬስ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG