በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊ ደራሲ ፕሊፕ ሮት በሰማኒያ አምስት ዓመቱ አረፈ


የበርካታ ሽልማቶች ባለቤቱ ዕውቁ አሜሪካዊ ደራሲ ፕሊፕ ሮት በሰማኒያ አምስት ዓመቱ አረፈ።

የበርካታ ሽልማቶች ባለቤቱ ዕውቁ አሜሪካዊ ደራሲ ፕሊፕ ሮት በሰማኒያ አምስት ዓመቱ አረፈ።

ሮት ከሃምሳ ዓመታት በላይ በዘለቀው የድርሰት ሕይወቱ የይሁዲ አሜሪካውያንን ተመክሮ የሚፈትሹ በርካታ ሥራዎቹን ጨምሮ ከሠላሳ በላይ መጽሐፍት ደርሷል።

እአአ በ1959 የታተመው የአጫጭር ልቦለድ ድርሰቶች ስብስብ የተካተተበት የመጀመሪያው መጽሐፉ ‘Goodbye Columbus’ ለብሔራዊ ሽልማት በቅቷል።

ከፍተኛ ተወዳጅት ያተረፈለት ልቦለድ ሥራው ታዲያ ከዚያ አሥር ዓመታት በኋላ የታተመው፤ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የሚወለድ አንድ የኒው ዮርክ ከተማ ነዋሪ ወጣት ታሪክ፣ የቁጥጥር አጠባቂ እናቱን እና ጾታ ነክ በሆኑ ጉዳዮች የሚዋጥበትን ጠባዩን የሚተርከው ‘Portnoy’s Complaint’ (በግርድፉ ወደ አማርኛ ሲመለስ የ ‘Portnoy’ ቅሬታዎች) የሚለው መጽሐፉ ነው።

‘American Pastoral’ በሚል ርዕስ የደረሰው ሌላው ተወዳጅ ልቦለድ ድርሰቱ እአአ በ1998 ለ‘Pultizer’ ሽልማት በቅቷል። ሌሎች ታላላቅ ሽልማቶቹ ‘Man Booker’ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የ’Pen/ Faulkner’ ሽልማት እና ብሔራዊ የኪነጥበብ ሥራዎች ሽልማት (National Medal of Arts) ይገኙበታል።

ሮት ባደረበት የልብ ሕመም ሲረዳ ከቆየ በኋላ በሚኖርባት የኒው ዮርክ ከተማ በትላንትናው ዕለት ማረፉን ጉዳይ አስፈፃሚው ይፋ አድርገዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG