በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በንግሥቲቱ የሃዘን ቀን የአውስትራሊያ ነባር ሕዝቦች ተቃውሞ አደረጉ


የተቃውሞ ሰልፍ በሲዲኒ
የተቃውሞ ሰልፍ በሲዲኒ

አውስትራሊያ የንግሥት ኤልሳቤጥ ሞትን ምክንያት በማድረግ የሃዘን ቀን አድርጋ ስትውል፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ነባር ሕዝቦች ዘውዳዊ አገዛዙንና በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ምክንያት የደረሰውን ችግር በማውገዝ በመላ ሃገሪቱ ዛሬ የተቃውሞ ሠልፍ አድርገዋል።

ለብዙ አውስትራሊያውያን ንግሥቲቱ “የእምነት የሚጣልበትና፣ የአስተማማኝነት” ምልክት ናቸው።

"በአውስትራሊያ ለሚገኙ ነባር ሕዝቦች ግን ንግሥቲቱ በእአአ 1788 እንግሊዞች ሲሰፍሩ መሬታቸው የተዘረፈበንት ጨካኝ የቅኝ ግዛት ዘመን ይወክላሉ" ይላል የቪኦኤው ፊል መርሰር ከሲድኒ በላከው ዘገባ።

አውስትራሊያ ከጋራ ብልጽግና ሀገሮች አንዷ መሥራችና፣ ህገመንግስታዊ የንጉስ አገዛዝ ሥርዓትን የምትከተል ሃገር ነች። ጥቅላይ ምኒስትር አንተኒ አልበኒዝ ዛሬ በተደረገው ሥነ ስርዓት ላይ ንግሥት ኤልሳቤጥን አሞግሰዋል። ሆኖም ግን “ዘውዳዊ አገዛዝ ይገርሰስ” በሚል በመላ ሃገሪቱ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።

አውስትራሊያ እአአ 1999 በተደረገ ሕዝበ-ውሳኔ ከእንግሊዝ የዘውድ አገዛዝ ጋር ያላትን ህገ መንግሥታዊ ትሥሥር ላለመተው መርጣለች።

XS
SM
MD
LG