በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውስትራሊያ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት መታሰቢያ በነባር ህዝቦች ዘንድ ውዝግብ አስነሳ


በሲድኒ የተካሄደ ሰልፍ
በሲድኒ የተካሄደ ሰልፍ

አውስትራሊያውያን ዛሬ የእንግሊዝን ቅኝ አገዛዝ 235ተኛ ዓመት መታሰቢያ እያከበሩ ነው። ይሁንና ከሕዝባዊ በዓላት አንዱ የሆነው የዚህ ዕለት መታሰቢያ አከባበር በአገሬው ነባር ሕዝቦች ላይ በደረሰ ኢፍትሃዊነት ከባድ ቁጣ በመቀስቀስ፣ ብሔራዊው ትኩረት በአካባቢው ቀደምት ነዋሪነት ለሚታዩት ሕዝቦች በአገሪቱ ሕገ መንግሥት እውቅና ይሰጥ ዘንድ በአዲሱ መንግሥት ላይ ግፊት እንዲደረግ ምክኒያት እየሆነ ነው።

በሌላ በኩል በርካታ ትላልቅ ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው በዕለቱ አለያም በምትኩ በመረጡት ሌላ ቀን እረፍት እንዲወስዱ ምርጫ መስጠት ጀምረዋል።

የአውስትራሊያም መንግሥት በበኩሉ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1788 በሲድኒ ባሕረ ገብ መሬት የእንግሊዝ ሰፋሪዎች ያችን ምድር የረገጡበትን ዕለት ለማሰብ ባንዲራ የሰቀሉባትን ቀን በማስታወስ የሚከበረውን ይህን በዓል አስመልክቶ ሕዝባዊ ቅሬታው እየጨመረ በመምጣቱ ለሰራተኞች ምርጫ እየሰጠ ነው።

በተጨማሪም በአውስትራሊያ የመጀመሪያዎቹን አውሮፓውያን አመጣጥ እና አሰፋፈር የሚመለከተው እና ውዝግብ ያልተለየው ታሪክ በአገሪቱ ፓርላማ ነባር ሕዝቦችን የሚወከል አካል የሚፈጠርበትን ሁኔታ የተመለከተ ክርክር ቀስቅሷል።

XS
SM
MD
LG