በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አን ሳን ሱ ቺ በሙስና ወንጀል ክስ እስራት ተፈረደባቸው


ፎቶ ፋይል፦ አን ሳን ሱ ቺ
ፎቶ ፋይል፦ አን ሳን ሱ ቺ

በወታደራዊው አገዛዝ ከመሪነት የተወገዱት የሚያንማሯ መሪ አን ሳን ሱ ቺ ከተመሰረተባቸው በርከት ያሉ የሙስና ወንጀል ክሶች በአንዱ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ብሏቸዋል። እስራት ተፈርዶባቸዋል።

የሰባ ስድስት ዓመቷ ሳን ሱ ቺ በአምስት አመት እስራት እንዲቀጡ ዛሬ ዋና ከተማዋ ናይፒታው ዳኛው ውሳኔ መስጠታቸውን ለፍርድ ሂደቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል። ችሎቱ የተካሄደው በዝግ ሲሆን ጠበቆቻቸው መግለጫ እንዳይሰጡ ታግደዋል።

ሳን ሱቺ ከብሄራዊ የዲሞራሲ ሊግ ፓርቲያቸው አባል እና የትልቋ ከተማ የያንጎን ዋና ሚኒስትር ከነበሩት ፊ ሚን ቲየን ስድስት መቶ ሺህ ዶላር በጥሪ ገንዘብ እና አስራ አንድ ኪሎ ወርቅ ጉቦ ተቀብለዋል ተብለው በቀረበባቸው ክስ ነው የተፈረደባቸው።

ወታደራዊው መንግሥት ሌሎችም አን ሳን ሱ ቺን የመንግሥት ሚስጥር ህግ መተላለፍ እና ሊሎችም በርካታ ክሶች የመሰረተባቸው ሲሆን በብዙዎቹ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል። በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ከተባሉ በጠቅላላው ከመቶ ዐመት በላይ እስራት ቅጣት ሊያስፈረድባቸው እንደሚችል ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG