አዲስ አበባ —
አዲስ አበባ ላይ ከነገ በስተያ ዐርብ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ይጀመራል፡፡
የጉባዔው መሪ ቃል “የሴቶችን የውሣኔ ሰጭነት አቅም የማጠናከር ዓመት እና የአፍሪካ የልማት ትልም የ2063 ዓ.ምን አጀንዳ ማጠናከሪያ” የሚል ነው፡፡
በጉባዔው ዝግጅትና ዋና ዋና አጀንዳ ላይ የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ኤራስተስ ሞኤንቻ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ለጋዜጣዊ መግለጫው ዝርዝር የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ፡፡