በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ መቀመጡ ትርጉም


አፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
አፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ በአካል እንዲካሄድ መወሰኑ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

ጉባዔው ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄዱ ሀገሪቱን ደኅንነት የሚያንፀባርቅ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ጉባዔውን እንድታስተናግድ መወሰኑ “የአፍሪካ መሪዎች ኢትዮጵያን የተሻለ እንደተረዷት የሚያሳይ ነው” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ዶ/ር መሰንበት አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ጉባዔውን ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መወሰኑን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባወጡት የፅሁፍ መልዕክት ‘ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም የተረዱ’ ያሏቸው የአፍሪካ መሪዎች ውሳኔውን በማሳለፋቸው አመስግነዋል፡፡

የሰሞኑ የእሥረኞች መፈታት ጉዳይ ለዚህ ውሳኔ አስተዋፅዖ ማበርከቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በኮቪድ -19 ምክንያት በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአካል ሲገናኝ ይህ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ መቀመጡ ትርጉም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00


XS
SM
MD
LG