በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት መርማሪ ኮሚሽን ሁለቱንም የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በጦር ወንጀል ከሰሰ


የደቡብ ሱዳን መንግስትና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር ታማኝ ኣማጽያን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል ይላል የኣፍሪካ ህብረት የደቡብ ሱዳን ግጭት መርማሪ ኮሚሽን ሪፖርት። መርማሪ ኮሚሽኑ የዘር ማጥፋት ተፈጽሙዋል ለማለት የሚያበቃ ማስረጃ ግን ኣላገኘንም ብለዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግስትና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር ታማኝ ኣማጽያን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል፡ አንዳንዱ በጦርነት ወንጀል ነው ያለው የኮሚሽኑ ሪፖርት ግድያ፡ ማሰቃየት፡ ጠለፋ፡ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎችም ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃት ጨምሮ ጭካኔ እና ኢሰብዓዊነት የተመላበት ጥቃት ፈጽመዋል ይላል። የዘር ማጥፋት ተፈጽሙዋል ለማለት የሚበቃ ማስረጃ ግን ኣላገኘንም ነው ያለው የአፍሪካ ህብረቱ መርማሪ ኮሚሽን።

ለተፈጸሙት ወንጀሎች ከሁለቱም ወገን በዋናነት ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉትን ለይተናል ሲልም ኣመልክቱዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት ባለስልጣናትን አስተያየት ለጊዜው ለማግኘት አልተቻለም። የደቡብ ሱዳን ነጻ ኣውጭ ሰራዊት SPLA የተቃዋሚው ኣንጃ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊው ኣምባሳደር ኢዚኪዬል ሎል ጋትኮዎት ግን ሪፖርቱ አማጽያኑን አያሳስብም። የሚፈልጉት በወንጀል ያለመጠየቅ ልማድ እንዲያከትም ነውና ብለዋል።

“በርግጥም ታስታውስ እንደሆነ የኔ ሊቀመንበር የSPLA የተቃዋሚው ኣንጃ መሪ ዶክተር ሪያክ ማቻር ከ2014 ጀምረው በሚያወጡዋቸው መግለጫዎች ሪፖርቱ እንዲወጣ ሲወተውቱ ከርመዋል። በጦርነቱ ወቅት ወንጀሎችን የፈጸሙ በተጠያቂነት እንዲያዙ ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ኣሁን ሪፖርቱ ወጥቱዋል ደስ ብሎናል።”

የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት በሁለቱም ወገኖች የተፈጸሙትን ግድያዎች ኣውግዙዋል። ኮሚሽኑ “በከፍተኛ ሚስጥር የሚያዝ የስም ዝርዝር” ሲል የፈረጀው ሰነድ ያለው ሲሆን ይፋ ባደረገው ረፖርቱ ውስጥ ግን ኣላካተተውም።

የደቡብ ሱዳን ቀውስ ስረ መሰረት የፖለቲካ ስልጣን ሽኩቻ፡ የተፈጥሮ ሃብቱዋን ገቢ ለመቆጣጠር የሚደረግ ትግል፡ ሙስናና በስልጣን በዝምድና መጠቃቀም መሆኑን ገልጾ የሀገሪቱ ሃብት የዋና ዋና የፖለቲካ መሪዎችና የቤተሰቦቻቸው መጠቀሚያ ሆንዋል ብሉዋል።

ከዋሽንግተን የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኛ ጄምስ ባቲ (James Butty) ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታየ አቅርባዋለች፣ ከተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአፍሪካ ህብረት መርማሪ ኮሚሽን ሁለቱንም የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በጦር ወንጀል ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00

XS
SM
MD
LG