በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርና የኮሚሽኑ ሊቀመንበር በዩክሬን ጉዳይ ጥሪ አሰሙ


የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የሴኔጎል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት “በጣም ብርቱና አደገኛ” ያሉት ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ “አብዝቶ እንደሚያሳስባቸው” አስታውቀዋል።

ሁለቱ የኅብረቱ መሪዎች ዛሬ፣ ሐሙስ ማምሻውን በጋራ ባወጡት መግለጫ የሩሲያ ፌዴሬሽንና ሌላም ማንኛውም አካባቢያዊና ዓለምአቀፍ ተዋናይ ዓለምአቀፍ ህግን ያለማቅማማት እንዲያከብር፣ የዩክሬንን የግዛት ጥብቅነትና ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲያከብር ጥሪ አድርገዋል።

የኅብረቱና የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቃነመንበር አክለውም ሁለቱም ወገኖች ፈጥነው ተኩስ እንዲያቆሙ፣ ዓለምን ከሁሉን አቀፍ ብጥብጥ መዘዝ ለመታደግና በዓለም ህዝቦች ሁሉ ስም፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥም ስለሰላምና መረጋጋት ሲባል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ያለመዘግየት የፖለቲካ ንግግር እንዲከፍቱ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከኅብረቱ ፅህፈት ቤት የወጣው መግለጫ- አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG