በአፍሪካ ሕብረት ፅ/ቤት ውሰጥ ዛሬ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ይፋ እንደተደረገው አፍሪካ የሚሌንየሙን የልማት ግቦች ለማሣካት በጀመረችው ጉዞ የተደበላለቁ ውጤቶች እየታዩ ነው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ በአፍሪካ ሕብረት፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በመንግሥታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም በሚዘጋጀው ዓመታዊ ሪፖርት እንደተመለከተው አፍሪካ ወደሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የምታደርገው ግሥጋሴ ባጠቃላይ ሲመዘን አጠቃላዩ ሂደት አዎንታዊ ነው፡፡
ከዕድገት አመላካቾችና ከየሃገሮቹ አኳያ ሲታይ ደግሞ በእንቅስቃሴው የተደበላለቀ ውጤት ይታያል፡፡
አሁን በሚታዩት አዝማሚያዎች መሠረት (እአአ) በ2015 ዓ.ም ይሣካሉ የተባሉትን የልማት ግቦች ለማሣካት ያለው የዕድገት ፍጥነት በቂ አይደለም፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡