በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል


የርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የቤኒኑ ፕሬዚዳንት እና አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ያዪ ቦኒና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጄከብ ዙማ በሰብዓዊ መብቶች ማዕከሉ የመሠረት ድንጋይ ላይ ሻማ ሲያበሩ
የርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የቤኒኑ ፕሬዚዳንት እና አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ያዪ ቦኒና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጄከብ ዙማ በሰብዓዊ መብቶች ማዕከሉ የመሠረት ድንጋይ ላይ ሻማ ሲያበሩ

በአፍሪካ ሕዝቦች ላይ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያስታውስ መታሰቢያ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃ በተሠራበት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚታነፀው መታሰቢያ ትኩረት አፍሪካዊያን መንግሥታት በሕዝቦቻቸው ላይ የፈፀሙትን በደል ማስታወስ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊ መብቶች መታሰቢያ ዓላማውን በግልፅ ዘርዝሮ ያስቀመጠው አንድ ኮሚሽኑ ያቋቋመው አማካሪ አካል ባለፈው ጥቅምት መገባደጃ ላይ ባካሄደው ስብሰባ ነበር፡፡

- የመታሰቢያውን ዋና ዋና ግቦች መንደፍ፤

- ለመታሰቢያው ቋሚ ሕንፃዎች ሥራ የሚሆን የንድፍ ውድድር የሚካሄድበትን መመሪያ ማርቀቅ፤

- ተሣትፎው የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ሰለባዎች ድርጅቶችና ቤተ-መዘክሮችን የመሣሰሉ አካላትን በስፋት ያካተተ እንዲሆን ማረጋገጥና የመሣሰሉትን ያጠቃልላል፡፡

የጊዜያዊው አማካሪ ቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ መታሰቢያው ምን ምን አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ለቪኦኤ ሲናገሩ “በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሕንፃ ውስጥ ወይም በቅጥር ግቢው የሚኖረው አገልግሎት በአሕጉሩ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች መታሰቢያዎችን ሁሉ የሚያገናኝ ይሆናል” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG