በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ምርጫ የተሳካ ነበር አለ፤ ተቋማት እንዲጠናከሩ መከረ


ኬቱሚሌ ማሲሬ
ኬቱሚሌ ማሲሬ

“ምርጫው የሕዝቡን ፍላጐት ያንፀባረቀ ነበር”

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞው የቦትስዋና ፕሬዝደንት ኬቱሚሌ ማሲሬ በግንቦት 15ኡ ምርጫ ድምጽ ሰጭዎች የሚፈልጉትን ፓርቲ እንዲመርጡ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ገልጸዋል።

ረቡእ ምሽት በአዲስ አበባ መግለጫ የሰጡት ማሲሬ “ምርጫው የተካሄደው የአገሪቱን የምርጫ አካሄድ በሚመሩት ህገ-መንግስታዊና ህጋዊ ማእቀፎች እንዲሁም ደምብና መመሪያዎች መሰረት ነው” ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ትዝብት ሪፖርት ምርጫው የተካሄደው ህብረቱ ለምርጫ አስፈላጊ ብሎ ካስቀመጣቸው መስፈርቶች አኳያ መሆኑን አትቷል።

“የ2002ኡ የኢትዮጵያ የህግ አውጭ አካል ምርጫ የህዝቡን ፍላጎት ያንጸባረቀ ነበር፤” ብልዋል ኬቱሚሌ ማሲሬ። “ኢትዮጵያዊያን ላሳዩት ሰላማዊ ሁኔታና የነቃ ተሳትፎ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል።”

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መስተካከል አለባቸው ያላቸውን አንዳንድ ጉዳዮችም ዘርዝሯል። ከነዚህም መካከል፡- የመራጭ ካርዶችና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመት እንዲሻሻል፣ የምርጫ ህጉ ተግባራዊ እንዲሆንና የማህበረሰብ ተቋማት ተሳትፎ እንዲጠናከር የሚሉ ይገኙበታል።

XS
SM
MD
LG