በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ አማጽያን የቀጥታ ግንኙነት እያደረጉ ነው” የአፍሪካ ሕብረት


“የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ አማጽያን የቀጥታ ግንኙነት እያደረጉ ነው” የአፍሪካ ሕብረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:31 0:00

“የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ አማጽያን የቀጥታ ግንኙነት እያደረጉ ነው” የአፍሪካ ሕብረት

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ አማጽያን "የቀጥታ ግንኙነት" እንደነበራቸው የአፍሪካ ሕብረት በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የነበሩትን ግንኙነቶችን አስመልክቶ ለመጀመሪያው ጊዜ ማረጋገጫ በሰጠበት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከአማፂያኑ ጋር የገባውን ከፍተኛ ግጭት ያስታወሰው የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ፣ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ሁለቱም ወገኖች ለ21 ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም የሚያግዝ ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ሲገልጹ መቆየታቸውን አትቷል። ይሁንና ኢትዮጵያ ማንኛውም ዓይነት ድርድር በአፍሪካ ሕብረት እንዲመራ ስትል ግፊት ስታደርግ፤ አማጽያኑ በበኩላቸው በሠላም ጥረቱ ንቁ ተሳትፎ በነበራቸው የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለቱን ወገኖች እንዲያደራደሩ ይፈልጋሉ።

እስካሁን የተደረሰበትን ለህብረቱ የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ያስረዱት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ግጭቱን ለማስቆም የታለመውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሃምሌ 27/2014 ዓ.ም በተጻፈ እና ምክር ቤቱ ትላንት ሐሙስ በድረ-ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል ተፈጸመ ላለው የቀጥታ ግንኙነት የሕብረቱን ከፍተኛ ተወካይ አወድሷል። የህብረቱ የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ምክር ቤት መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የቀጥታ ግንኙነት መደረጉን በይፋ ያረጋገጠ የመጀመሪያው መረጃ ነው።

የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አያይዞም የድርጅቱ መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ውይይት ከመጀመሩ አስቀድሞ በክልሉ የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት መጀመር አለበት ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል።

የአፍሪካ ሕብረት ምክር ቤት በተጨማሪም “ተፋላሚዎቹ ወገኖች ከምንም በላይ የኢትዮጵያንና የህዝቦቿን ጥቅም በማስቀደም ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይትን የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደ ብቸኛው አዋጭ መንገድ መቀበል አለባቸው” ሲል ጥሪ አድርጓል።

“በኢትዮጵያ ላለው ሁኔታ በኦባሳንጆ መሪነት የተያዘውን ጥረት ‘በድርድር የሚደረስ ዘላቂ መፍትሄ’ ለማምጣት ብቸኛው አዋጭ እና ውጤታማ አቀራረብ በመሆኑ፣ በአፍሪካ ሕብረት ለሚመራው የሽምግልና ሂደት የሚሰጡትን ድጋፍ ከፍ እንዲያደርጉ” ሲል አቀፍ አጋሮቹን አሳስቧል።

የሰብአዊ እርቅ ከታወጀበት እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ካለፈው መጋቢት መጨረሻ አንስቶ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት መረጋጋት ማሳየቱን እና ይህም ቁጥሩ ስድስት ሚሊዮን ለሚደርሰው የትግራይ ህዝብ በእጅጉ የሚያስፈልገው ዓለም አቀፍ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪኖች ዳግም እንዲንቀስቀሱ ማስቻሉን አመልክቷል።

ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ለምግብ እጥረት መዳረጉን እና የመብራት፣ የመገናኛ እና የባንክ አገልግሎቶችን የመሳሰሉት መሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት መገደቡንም ዘገባው ጨምሮ አስታውሷል።

አማጽያኑ ከዚያ በሚገኘው የፌዴራሉ ሰራዊት ጦር ካምፕ ላይ ጥቃት መሰንዘረቸውን በመጥቀስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በህዳር 2020 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦራቸውን ማዝመታቸውን፣ ከዚያም ባለፈው ዓመት የሰኔ ወር ህወሓት መልሶ ትግራይን በመቆጣጠር ጦርነቱ ዳግም እስከተገታበት ድረስ ወደ አጎራባቹ የአፋር እና አማራ ክልሎች ያስፋፋውን ጦርነት መክፈቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘርዝሯል።

XS
SM
MD
LG