በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት በሶማልያ ከተመድ ኃይሎች ጋር ለመሰማራት ወሰነ


ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ህብረት
ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ህብረት

የአፍሪካ ህብረት በሶማልያ ያለውን ተልእኮ የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ህብረት በጥምረት ወደ ሚያካሂደቱ የጋራ ተልእኮ ለማሸጋገር መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የደህንነት ምክር ቤት፣ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ ከአፍሪካ ህብረትና ከተባበሩት መንግሥታት የተውጣጣው አካል፣ ለሶማልያ የተሻለ መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የሶማልያ መንግሥት፣ ሀሳቡን ቀደም ሲል ተቃውሞ የቆየ ሲሆን፣ መጀመሪያ በአፍሪካ ህብረት እየታገዘ ከቆየ በኋላ፣ ቀስ በቀስ የሶማልያ መንግስት ወደሚቆጣጠረው አካል ይዛወራል የሚል እምነት እንደነበረው ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ህብረት፣ በሶማልያ ጉዳይ ተሳታፊ ከሆኑ አገሮች ጋር፣ መመካከር እንደሚፈልግ ጨምሮ ያስታወቀ ሲሆን፣ አሁን ያለው የወታደሮች ቁጥርም መጨመር ያለበት መሆኑንም ጠቁማል፡፡

አሁን በሶማልያ ሰላም አሰከባሪ ኃይሎቻቸውን ያሰማሩ 5 አገሮች፣ ኢትዮጵያ፣ ዩናጋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ኬንያና ጅቡቲ ናቸው፡፡

በሶማልያ የተሰማሩት ከ19ሺ በላይ ጦር የሚሆኑት የህብረቱ ወታደሮች አሚሶን በመባል ይታወቃሉ፡፡

ህብረቱ በሶማሊያ መሪዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠረ ያለው ልዩነት ያስከፋው መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG