ዋሺንግተን ዲሲ —
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትም በኢትዮጵያና በኤርትራ ግንኙነት እየታዩ ያሉት አዎንታዊ ዕርምጃዎች በደስታ ተቀብለናል ብለዋል።
የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የወሰዷቸውን ደፋር እና ጠንካራ ዕርምጃዎች እደንቃለሁ ያሉት የሕብረቱ ኮምሺን ሊቀመንበር በሁለቱ ሀገሮች መካከል አዲስ የመልካም ጉርብትና ምዕራፍ እንዲጀመር በጀመሩት ጎዳና ፀንተው እንዲቀጥሉ አበረታታለሁ ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ