የፕሪቶርያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ፣ ሁለተኛ ዙር ስትራቴጂያዊ ግምገማ መካሔዱን የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡
ግምገማው፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በሚካሔደው የፖለቲካ ውይይት ላይ ያተኮረ እንደነበረ ኅብረቱ ገልጿል፡፡
የስምምነቱ ፈራሚዎች፥ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት የመመለስ፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ የማዋሐድ ተግባራትን ደረጃ በደረጃ ማስፈጸማቸውን ለመቀጠል እንደተስማሙ ኅብረቱ በመግለጫው አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም