በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ የተፈፀመው የመንግሥት ለውጥ ተወገዘ


የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ በማሊ ህገ መንግሥት በጣሰ መነግደ የተፀመውን የመንግሥት ለውጥ አወገዙ።

ራማፎሳ ትናንት ረቡዕ ባወጡት መግለጫ ያመፁት ወታደሮች ያሰሩዋቸውን የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቡቡ ሲሴን እና ሌሎችም ባለሥልጣናት እንዲለቁ ጠይቀዋል።

ራሳቸውን የማሊ ህዝብ አድነት ብሄራዊ ኮሚቴ ብለው የሚጠሩት ወታደሮች ምርጫ የሚካሄድበት መንገድ ላይ የምንሰራ ይሆናል ከማለት ባለፈ ያሉት ነገር የለም።

ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን መልቀቃቸውን ባስታወቁበት ንግግራቸው ብሄራዊ ሸንጎውና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራዊ የመንግሥት ካቢኔ ፍርሷል ብለዋል።

ዓለምቀፉ ማኅበረሰብ ለማሊ ህዝብ ሲቪላዊ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲመለስለት እንዲረዳ የህብረቱ ሊቀ መንበር ተማፅነዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ማሊ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ እስኪመለስ የታሰሩት ባለሥልጣናትም እስኪፈቱ ከህብረቱ ታግዳለች ብለዋል።

XS
SM
MD
LG