በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በቬንዙዌላ


ዋና ከተማዋ ካራካስ ውስጥ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ ነው ሲል ዛሬ የቬንዙዌላው ሶሺሊስት መንግሥት ተናገረ።

መንግሥቱ ይህን ያለው ራሳቸውን የሽግግር መሪ አድርገው የሰየሙት ተቃዋሚ መሪው ሁዋን ጉዌዶ የፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን መንግሥት ለመገልበጥ በያዝኩት ጥረት ከጎኔ ናቸው ካሏቸው የጦር ሰራዊት ወታደሮች ጋር ጎዳና ላይ በወጡበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት ጉዌይዶ “ህገ መንግሥቱን የሚደግፉ ጀግኖቹ ወታደሮች፣ ጀግኖቹ ሃገር ወዳዶች ጀግኖቹ ወንዶች እነሆ ዛሬ ለጥሪያችን መልስ ሰጥተዋል”ብለዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ሆርሄ ሮድሪጌዝ ግን በአሁኑ ወቅት የመፍንቅለ መንግሥት ሙከራ ለመደገፍ አንድ የጦር ካምፕ አጠገብ ያደፈጡ ጥቂት ከሃዲ የጦር ሰራዊት አባላትን ድርጊት ለማምከን እየተንቀሳቀስን ነንብለዋል። ህዝቡ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ለምክሸፍና ሰላም ለማስከበር ከሚኒቀሳቀሰው የጦር ሰራዊታችን ጎን በከፍተኛ ተጠንቀቅ እንዲቆም እንማፀናለን ሲሉም ሚኒስትሩ አክለው አሳስበዋል።

የማዱሮ ደጋፊዎች ከጦር ካምፑ ፊት ለፊት ለተሰባሰቡት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ አለቃሽ ጋዝ ተኩሰዋል። ይሁን እንጂ በቴሌቭዥን ሲታይ ወታደሮቹና የተቃዋሚ መሪው ጉዋይዶ ደጋፊዎች በጦር ካምፑ ያለሥጋት ሲንጎራደዱ ተስተውለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG