በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአብዬ በደረሰ ጥቃት 32 ሰዎች ሞቱ


በሱዳንና በደቡብ ሱዳን ሀገራት የይገባኛል ጥያቄ በሚቀርብባት በአብዬ ግዛት በተፈጸመ ጥቃት፣ 32 ሰዎች እንደተገደሉ፣ የግዛቲቱ መንግሥት ተወካይ አስታውቀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የምትገኘውና በነዳጅ የበለጸገችው ግዛት መንግሥት ተወካይ፣ ትላንት እሑድ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል። ጥቃቱን የፈጸሙት፣ የደቡብ ሱዳንን ሠራዊት መለዮ የለበሱ ሚሊሺያዎች ናቸው፤ ተብሏል።

ከጥቃቱ ሰለባዎች ውስጥ፣ በቤታቸው ሳሉ በእሳት ተቃጥለው ሕይወታቸውን ያጡ ሴቶች እና ሕፃናት እንደሚገኙበትና ከኻያ በላይ ሰዎችም እንደተጎዱ፣ የአብዬ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒስትር እና በግዛቲቱ የደቡብ ሱዳን ተወካይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አንድ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባልም፣ ከሟቾቹ አንዱ እንደኾኑ ታውቋል።

በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል የምትገኘው አብዬ ግዛት፣ ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጀምሮ ተደጋጋሚ ግጭት ሲስተዋልባት ቆይቷል።

በአብዬ፣ አራት ሺሕ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ሲገኝ፣ የጸጥታው ም/ቤትም በቅርቡ የሥራ ዘመኑን እንዳራዘመ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG