በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና - በካታር ዶሃ

ዛሬ በካታር ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለግማሽ ፍፅሜ እና ፍፃሜ አልፈዋል። በ17ኛው የዓለም ሻምፕዮና ለኢትዮጵያ የመጀመርያ በሆነው የሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ድርቤ ወልተጂ በተወዳደረችበት ምድብ አራት 02፡02.71 ደቂቃ በመግባት አምስተኛ ሆና አጠናቃለች። ሆኖም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፕዮኗ ከተሸናፊዎች ፈጣን ሰዓት ባስመዘገበ በሚለው ህግ ነገ መስከረም 17/2012 ዓ.ም ለሚካሄደው ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።

በሴቶች 3000ሜ መሰናክል የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ መቅደስ አበበ የግሏን ፈጣን ሰዓት በማስመዝብ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚደረግው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች።
በወንዶች 5000ሜ ያለፈው የዓለም ሻምፕዮኑ ሙክታር ኢድሪስ፣ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ጥላሁን ሃይሌ፣ እንዲሁም ሰለሞን ባርጋ ለፍፃሜ ውድድሩ አልፈዋል። አባዲ ሃዲስ አልተሳካለትም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG